+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የቀጨኔ ቁስቋም የአስፋልት መንገድ ግንባታ ቀሪ ሥራ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4 ቀን 2015፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በራስ አቅም እየገነባቸው ከሚገኙ በርካታ የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነውን የቀጨኔ ቁስቋም የአስፋልት መንገድ ፕሮጀክት ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡

የቀጨኔ ቁስቋም የአስፋልት መንገድ ፕሮጀክት በአጠቃላይ 1 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና 16 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ ከቀጨኔ መስመር ተነስቶ ወደ ሽሮ ሜዳ – ቁስቋም የሚያገናኝ አቋራጭ መንገድ ነው፡፡

የፕሮጀክቱ የግንባታ ስራ አሁን ላይ ከአጠቃላይ የመንገዱ ክፍል 1 ነጥብ 3 ኪሎ ሜትር አስፋልት የለበሰ ሲሆን፣ ቀሪውን የመንገድ ክፍል ጨምሮ የእግረኛ መንገድ ፣ የድጋፍ ግንብ እና ተያያዥ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ ሙሉ ለሙሉ አጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ሲደረግ የአካባቢውን ህብረተሰብ በመንገድ መሰረተ ልማት ተጠቃሚነት ከማሳደጉም በላይ ከቀጨኔ ወደ ሽሮ ሜዳና አካባቢው በአጭር ርቀት ለመጓዝ የሚያስችል ይሆናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.