የመንገድ መብራቶችን የማሻሻል ሥራ
የመንገድ ዳር መብራቶች በምሽት የሚኖረውን የህብረተሰቡን እንቅስቃሴ እና የትራፊክ ደህንነቱን ለማስጠበቅ ካላቸው ሚና ባሻገር የከተማዋን ገፅታ በመለወጥ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አላቸው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በአሁኑ ወቅት በከተማዋ የኤልኢዲ አምፑሎችን የመግጠም ሥራ በስፋት እያከናወነ ከመሆኑም ባሻገር ብልሽት ያጋጠማቸውን እየጠገነ ይገኛል፡፡
ባለስልጣኑ በ2015 የበጀት ዓመት ብቻ በስርቆትና በተሽከርካሪ ግጭት ምክንያት ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ 15 ሺህ 585 የመንገድ ዳር መብራቶችን የመጠገንና የማሻሻል ስራ ሰርቷል፡፡
• ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመዲናችን የሚተከሉ የመንገድ መብራቶች የኤል ኢ ዲ መብራቶች ናቸው፡፡
• እነዚህ የኤል ኢዲ አምፑሎች ወጪ ቆጣቢ ከመሆናቸው ባለፈ ብልሽት ሲያጋጥማቸው በአነስተኛ ወጪ የሚጠገኑ ናቸው፡፡
• አምፑሎቹ በአየር ላይ የሚዘረጋ የኤሌክትሪክ ኬብል ስለሌላቸው አደጋ የማድረስ እድላቸውም አነስተኛ ነው፡፡
• ኤል ኢዲ አምፑል የተገጠመላቸው የመንገድ መብራቶች የብርሃን አድማሳቸው ከፍተኛ በመሆኑም ለከተማዋ ተጨማሪ ውበትን የሚያላብሱ ሆነዋል፡፡
• የትራፊክ አደጋና፣ ስርቆት እንዲሁም የመንገድ ማስፋፊያ ስራዎች ለበርካታ የመንገድ መብራቶች ከጥቅም ውጪ መሆን ተጠቃሽ ምክንያቶች ናቸው፡፡