በበጀት ዓመቱ 29 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ ተገንብቷል
አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 2 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በ2015 በጀት ዓመት 29 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ መልሶ ግንባታ አከናውኗል፡፡
ባለሥልጣን መስሪያቤቱ በእግረኛ መንገድ የመልሶ ግንባታ ስራ ላይ በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ 17 ማህበራትን በማሳተፍ ለበርካታ ዜጎች የሥራ እድል እንዲፈጠር አድርጓል፡፡
በበጀት ዓመቱ የእግረኛ መንገዶች የመልሶ ግንባታ ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል ከጊዮርጊስ አደባባይ – አፍንጮ በር፣ ከጦር ኃይሎች – መንዲዳ፣ ከበድሉ ህንፃ- ኮሜርስ፣ ከካዛንቺስ መብራት – ዮርዳኖስ ሆቴል፣ ከአሮጌው ፖስታ ቤት – አትክልት ተራ፣ ከፓርላማ – ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስትያን፣ ከሜቴክ – ተማም ህንፃ ፣ ከአራት ኪሎ – ደጎል አደባባይ እና ሌሎች አካባቢዎችም ይገኙበታል፡፡
ባለስልጣኑ የሚገነባቸው የእግረኛ መንገዶች ሁሉንም የመንገድ ተጠቃሚዎች ታሳቢ ያደረገ ሲሆን፣ የእግረኛ መንገዶች ተሻሽለው መገንባታቸው የከተማዋ ውብ ገፅታ ከማላበሳቸውም በተጨማሪ የእግረኞችን እንቅስቃሴ ምቹ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity