+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የእግረኛ መንገዶችን ከጉዳት መከላከል የሁላችንም ኃላፊነት ሊሆን ይገባል!

በመዲናችን አዲስ አበባ በከፍተኛ የመንግሥትና የህዝብ ሀብት የተገነቡ የእግረኛ መንገዶች ከተገነቡበት ዓላማ ውጭ ባልተገባ መልኩ ጥቅም ላይ እየዋሉ በመሆናቸው ለከፍተኛ ጉዳት እየተጋለጡ ይገኛሉ።

በጋራ ሀብታችን የተገነቡትን እነዚህን የእግረኛና ሌሎች መንገዶችን በጋራ በመጠበቅና በመንከባከብ ረገድ የሁሉም ግብር ከፋይ ማህበረሰብ ኃላፊነት በመሆኑ ሁላችንም የዜግነት ድርሻችንን ልንወጣ ይገባል፡፡ በመሆኑም ማንኛውም ሠው በየትኛውም የመንገድ ሀብት ላይ ለሚያጋጥሙ ጉዳቶች በነፃ የስልክ መስመር 8267 ላይ በመደወል ጥቆማ መስጠት የሚችል መሆኑን ባለስልጣኑ ያስታውቃል፡፡

በተጨማሪም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ህገወጥ ተግባር በሚፈፀሙ ግለሰቦች ላይ አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ በመውሰድ ህግና ሥርዓት እንዲያስከብሩ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ያሳስባል።

Comments are closed.