+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በ2016 በጀት ዓመት ከ3 ሺ 500 በላይ ለሚሆኑ የባለሥልጣኑ ሠራተኞች ስልጠና ለመስጠት ታቅዷል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በ2016 በጀት ዓመት ከ 3 ሺ 500 በላይ ለሚሆኑ የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞ የስራ ላይ ስልጠና ለመስጠት መታቀዱን አስታወቀ፡፡

በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የስልጠና ማዕከል ኃላፊ አቶ መስፍን ከበረ በበጀት ዓመቱ የሠራተኞችን ፍላጎት መሰረት በማድረግ 74 በሚሆኑ የሥልጠና ርዕሶች ላይ ስልጠና ለመስጠት ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ተግባር መገባቱን ገልፀዋል፡፡

አሁን ላይ በግዥ መርሆች እና በፕሮጀክት አስተዳደር ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎች ለተቋሙ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች እየተሰጠ ሲሆን፣ በበጀት ዓመቱ ሊሰጡ የታቀዱ ልዩ ልዩ ሥልጠናዎች በአሰራር ሂደት ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖራቸውም አቶ መስፍን ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የሠራተኛውን እውቀት፣ አመለካከትና ክህሎትን ሊያሳድጉ የሚችሉ ስልጠናዎችን በመስጠት የተቋሙን የመፈፀም አቅም ማሻሻል ያስፈልጋል ያሉት ዳይሬክተሩ፤ ባለሰልጣን መስሪያ ቤቱ በራስ አቅም፣ በግዥና በባለድርሻ አካላት ትብብር የሠራተኛውን የስልጠና ፍላጎት ለማሟላት እንደሚሠራ ጠቁመዋል፡፡

የባለሥልጣን መስሪያቤቱ ሠራተኞች በበጀት ዓመቱ በሚዘጋጁ ልዩ ልዩ በስልጠናዎች ላይ በንቃት በመሳተፍ አቅማቸውን እንዲያጎለብቱና በስልጠና ወቅት በሚገበዩት እውቀትና ክህሎት በመታገዝ የተቋሙን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት እንዲረባረቡ አሳስበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.