+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በበጀት ዓመቱ ከ7 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የመንገድ ሀብት ላይ ጉዳት ደርሷል

አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም፡- በ2015 በጀት ዓመት በተሸከርካሪዎች ግጭት ምክንያት 7ከ ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ባለው የመንገድ መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

በበጀት ዓመቱ በቀለበት መንገድ ላይ 135፣ ከቀለበት መንገድ ውጪ ደግሞ 199፣ በድምሩ 334 የግጭት አደጋዎች ደርሰዋል፡፡

በተሽከርካሪዎች ግጭት በአብዛኛው ጉዳት እየደረሰባቸው የሚገኙት የመንገድ መብራት ምሶሶዎች፣ የትራፊክ ምልክቶች፣ የአቅጣጫና ርቀት አመላካች ሰሌዳዎች፣ የእግረኛ መከላከያ አጥሮች፣ የመንገድ አካፋይ ከርቭስቶን እና የማንሆል ክዳኖች ናቸው፡፡

በተሽከርካሪ ግጭት ሳቢያ እየደረሰ ላለው የመንገድ ሀብት ጉዳት መንስኤ ከሆኑት መካከል ጠጥቶ ማሽከርከር፣ ከፍጥነት ወሰን በላይ መንዳት እና ያለ መንጃ ፈቃድ ማሽከርከር ተጠቃሽ ናቸው።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በመንገድ ሀብት ላይ ጉዳት ካደረሱ አሸከርካሪዎች ተገቢውን የካሣ ክፍያ ከመሰብሰብ ጎን ለጎን ጉዳት የደረሰባቸውን የመንገድ ሀብቶች በመጠገን ላይ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.