በበጀት ዓመቱ ከ421 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የግንባታ ግብዓቶች ተመርተው ጥቅም ላይ እንዲውሉ ተደርጓል
አዲስ አበባ፣ሀምሌ 24 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በ2015 በጀት ዓመት ውስጥ ከ421 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ልዩ ልዩ የግንባታ ግብዓቶችን አምርቶ ጥቅም ላይ እንዲውሉ አድርጓል፡፡
ባለስልጣኑ ባለፉት 12 ወራት ውስጥ ካመረታቸው የግንባታ ግብዓቶች መካከል 132 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ የካባ ምርቶች፣ 111 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው የሲሚንቶ ውጤቶች እና 178 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የአስፋልት ኮንክሪት ውጤቶችን በራሱ ዓቅም አምርቶ ለተለያዩ የግንባታና ጥገና ስራዎች ጥቅም ላይ እንዲውሉ አድርጓል፡፡
በተጠናቀቀው የ2015 በጀት ዓመት ውስጥ አጠቃላይ ከ499 ሺ ሜትር ኪዩብ በላይ ገረጋንቲ፣ ሰብ ቤዝ፣ ቤዝኮርስ፣ ጠጠሮች፣ ነጭ ድንጋይ፣ ቀይ አሸዋ፤ ከ42 ሺ ቶን በላይ የአስፋልት ምርቶች፤ ከ18 ሺ 200 ሜትር በላይ የተለያዩ ቱቦዎች፤ 6ሺ 357 ካሬ ታይልስ፣ 41 ሺ 775 ብሎኬት፣ ማንሆል ክዳንና ኮንክሪት ፖል ፤ ከ1 ሺ 400 በላይ ከርቭ ስቶን እንዲሁም 12 999 ሜትር ኪዩብ የሲሚንቶ ኮንክሪት ምርቶች ተመርተው በራስ ኃይል ለሚከናወኑ የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ስራዎች ላይ እንዲውሉ ተደርጓል፡፡
የግንባታ ግብዓቶቹ በራስ አቅም መመረት መቻላቸው ባለስልጣኑ እያከናወናቸው ለሚገኙ የተለያዩ የግንባታና የጥገና ስራዎች የግብዓት እጥረት እንዳይፈጠር ትልቅ አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity