+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ባለስልጣኑ በበጀት ዓመቱ 823 ኪሎ ሜትር ልዩ ልዩ የጥገና ስራዎችን አከናወነ

ሀምሌ 22 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የሕብረተሰቡን የመንገድ መሠረተ ልማት ፍላጎት ለማሟላት ከአዳዲስ የመንገድ ግንባታ ስራዎች በተጨማሪ የመንገዶችን የአገልግሎት ደረጃን ለማሻሻል የሚያስችሉ ሁለገብ የመንገድ ጥገና ስራዎችን አከናውኗል፡፡

ባሳለፍነው በጀት ዓመት 611 ኪሎ ሜትር ልዩ ልዩ የመንገድ ጥገና ስራዎችን ለማከናወን አቅዶ 823 ኪ.ሜትር አከናውኗል፡፡ ይህም ከዕቅድ በላይ መከናወኑን ያሳያል፡፡ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የ2015 በጀት ዓመት አጠቃላይ የጥገና ስራዎች አፈፃፀም ከ2014 በጀት ዓመት አፈፃፀም 698 ጋር ሲነፃፀር በ15 በመቶ ብልጫ እንዳለው ያሳያል፡፡

በበጀት አመቱ 106 ኪ/ሜትር የአስፋልት መንገድ፣ 43 ኪ/ሜትር የጠጠር መንገድ፣ 69 ኪ/ሜትር የኮብል ስቶን፣ 405 ኪ/ሜትር የድሬኔጅ መስመር ጽዳት እድሳትና ጥገና፣ 17 ኪ/ሜትር የእግረኛ መንገድ ጥገናና የከርቭ ስቶን፣ 6 ኪ/ሜትር የእግረኛ መከላከያ አጥር ስራ እና ጥገና ስራዎች ተከናውነዋል፡፡ በተጨማሪም በቁጥር 26 ድልድይና የድጋፍ ግንብ ጥገና እንዲሁም የትራፊክ ሴፍቲ የጥገና ስራዎች እና የምሽት የትራፊክ እንቅስቃሴ ምቹና ደህንነቱ የተጠበቀ በማድረግ ረገድ የመንገድ ዳር መብራት የማዘመን እና የጥገና ስራዎች ተከናውነዋል፡፡

አጠቃላይ የጥገና ስራዎቹ በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ረጅም ጊዜ በማገልገል እና በአያያዝ ጉድለት የተጐዱ የመንገድ መሠረተ ልማቶችን እንደ ጉዳት መጠናቸው በመልሶ ግንባታ ደረጃ እና ቀላል ጥገና የሚፈልጉትን በመለየት የተከናወነ ነው፡፡ ይህም ሰፊ የጥገና ስራዎች በማከናወን የመንገዶችን አገልግሎት ደረጃ ማሳደግ እና ትራፊኩን በተሻለ መጠን የተሳለጠ እንዲሆን አስችሏል፡፡ የጥገና ስራው በዋና ዋና፣ በአቋራጭ እና የውስጥ ለውስጥ መንገዶች እንዲሁም በቀለበት መንገድ ላይ ተከናውኗል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.