+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

“አጠናቀን የምናስመርቃቸው ፕሮጀክቶች ለህዝቡ የገባነውን ቃል በተግባር እየፈፀምን ለመሆናችን በቂ ማሳያዎች ናቸው!” ወ/ሮ እናትአለም መለሰ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በነገው እለት የተለያዩ ተገንብተው የተጠናቀቁ የልማት ፕሮጀክቶችን ለአገልግሎት ክፍት ያደርጋል፡፡

በከተማ አስተዳደሩ ካፒታል በጀት ተገንብተው በነገው እለት ለአገልግሎት ክፍት የሚሆኑት ፕሮጀክቶች በ11ዱም ክ/ከተሞች የተሰሩ 72 የትምህርት ማዕከላት እና 28 የጤና ተቋማት መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እናትአለም መለሰ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገፀዋል።

ኃላፊዋ በመግለጫቸው እንደገለፁት፣ የከተማ አስተዳደሩ የማህበረሰቡን ፍላጎትና ጥያቄዎች መነሻ በማድረግ ለጤናው እና ለትምህርት ዘርፍ በሰጠው ልዩ ትኩረት በ2015 የበጀት ዓመት ሰፋፊ ስራዎችን አከናውኗል ብለዋል፡፡

በዚህም በነገው እለት ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ለሚሆኑት 100 የትምህርት እና የጤና ተቋማት ፕሮጀክቶች በከተማ አስተዳደሩ ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ የካፒታል በጀት ፈሰስ የተደረገባቸው መሆናቸው ተገልጿል።

የከተማ አስተዳደሩ በነገው እለት ለአገልግሎት ክፍት ከሚደርጋቸው 72 የትምህርት ማዕከላት መካከል 16ቱ ቅድመ መደበኛ፣ 36ቱ አንደኛ ደረጃ እንዲሁም 20ዎቹ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መሆናቸው መግለጫው ተገልጿል።

Comments are closed.