+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ባለስልጣን መስሪያቤቱ በበጀት ዓመቱ ከአንድ ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ግንባታና የጥገና ስራዎች አከናውኗል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በ2015 በጀት ዓመት በአጠቃላይ 866.11 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ልዩ ልዩ የመንገድ ግንባታና የጥገና ስራዎች ለመስራት አቅዶ 1 ሺህ 13 ነጥብ 52 ኪሎ ሜትር በመፈፀም ከዕቅዱ በላይ ማሳካት ችሏል፡፡

በበጀት ዓመቱ ከተከናወኑ የመንገድ ግንባታ ስራዎች መካከል 37.22 ኪሎ ሜ የአስፋልት፣ 26.58 ኪ.ሜ የጠጠር፣ 11.58 ኪ.ሜ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ የኮብል መንገዶች እና በሌሎች አካባቢዎች 84.8 ኪ.ሜ የኮብል ንጣፍ ሥራ አከናውኗል።

ከዚህ በተጨማሪም 29 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድመልሶ ግንባታ፣ 1.15 ኪ.ሜ የዲሬኔጅ መስመሮች ዝርጋታ እና 0.20 ኪ.ሜ የድጋፍ ግንብ ስራዎች፤ በድምሩም 190.53 ኪ.ሜ የሚሸፍን ልዩ ልዩ የመንገድ ግንባታ ሥራዎች አከናውኗል፡፡

በተመሳሳይ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከግንባታ ስራዎች ጎን ለጎን በተለያዩ ምክንያቶች ለብልሽት የተዳረጉ 106.3 ኪ.ሜ የአስፋልት፣ 42.6 ከ.ሜ የጠጠር፣ 69 ኪ.ሜ የኮብል፣ 391.94 ኪ.ሜ የድሬኔጅ መስመሮች ፅዳት፣ 11.72 ኪ.ሜ የድሬኔጅ መስመር ዕድሳትና ጥገና፣ 5.96 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ መከለያ አጥር

ስራ ከማከናወኑም ባሻገር 0.02 ኪ.ሜ የድጋፍ ግንብ ጥገና፣ 17.07 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ ጥገናና የከርቭ ስቶን ስራዎች ተሰርተዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ባለስልጣኑ 178.38 ኪ.ሜ የመንገድ ቀለም ስራዎችን በማከናወን በጠቅላላው 822.99 ኪ.ሜ የሚሆን ልዩ ልዩ የመንገድ ጥገና ስራዎችን በበጀት ዓመቱ ውስጥ አጠናቆ ለትራፊክ ክፍት አድርጓል፡፡

በተመሳሳይ 15 ሺህ 585 የመብራትና አምፖል ጥገና ስራዎችም በበጀት ዓመቱ ከተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ውስጥ የሚካተቱ ናቸው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.