+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በወንዞች ዳርቻና በድልድዮች ሥር የሚደፋው ቆሻሻና የግንባታ ተረፈ ምርት ባስከተለው ጎርፍ መንገዶች ለጉዳት እየተጋለጡ ነው

በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች በወንዝ ዳርቻዎችና በድልድዮች ሥር በተደጋጋሚ በሚደፋ ቆሻሻና የግንባታ ተረፈ-ምርት ሳቢያ የወንዝ ውሃ ወደ መንገድ በመውጣት የትራፊክ እንቅስቃሴውን እያስተጓጎለ ከመሆኑም በተጨማሪ የመንገድ አካላትን ለብልሽት እየዳረገ ይገኛል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ላይ ተመሳሳይ ችግር ከተከሰተባቸው አካባቢዎች መካከል ከቦሌ ወደ መገናኛ በሚወስደው ቀለበት መንገድ ላይ አያት ሆስፒታል አካባቢ ከሚገኘው ድልድይ ወደ ዋናው መንገድ የወጣው ጎርፍ እና በተመሳሳይም በጐተራ ማሳለጫ የታችኛው መተላለፊያ መንገድ ላይ የተከሰተው ጎርፍ ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በእነዚህ እና በሌሎች አካባቢዎች በሳምንቱ የተከሰቱ የዝናብ ውሃ ፍሰት መስተጓጎል ችግሮችን የፈታ ሲሆን፣ በሌሎች የጎርፍ አደጋ ስጋት ስጋት ባለባቸው አካባቢዎችም የመፍትሄ እርምጃ እየወሰደ ነው፡፡

በከተማዋ በልዩ ልዩ የኮንስትራክሽን ሥራዎች ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ አካላትም ከግንባታ ሳይቶች የሚያስወግዷቸውን ተረፈ ምርቶች በአግባቡ እንዲያጓጉዙ እና በመንገድ ሀብት ላይ ጉዳት ከሚያደርሱ ድርጊቶች እንዲታቀቡ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በጥብቅ ያሳስባል፡፡

በተመሳሳይም ደረቅ ቆሻሻዎችን በድልድዩች ሥርና በድሬኔጅ መስመሮች ላይ የሚደፉ ግለሶችን በመከታተል በህግ ተጠያቂ በማድረግ በኩል የደንብ ማስከበር አባላት እና በየደረጃው ያሉ የአስተዳደር አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ ባለሥልጣን መስሪያቤቱ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.