+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በክረምት ወቅት ሊከሰት የሚችለውን የጎርፍ አደጋ ስጋት የመከላከል ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል

ሐምሌ 13 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ናቸው ተብለው በተለዩ አካባቢዎች በልዩ ልዩ ግንባታና ጥገና ሥራዎች የመፍትሄ እየሰጠ ሲሆን፣ ከዚሁ ጎን ለጎን በየጊዜው በሚደፋ ደረቅ ቆሻሻና የግንባታ ተረፈ ምርት ምክንያት በደለል የተሞሉና ተገቢውን አገልግሎት መስጠት ባልቻሉ ድልድዮች ሥር የተከማቸውን ደለል እየጠረገ እና ቆሻሻ እያነሳ ይገኛል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሰሞኑን በድልድዮች ዙሪያ የደለል ጠረጋና የወንዝ ውሃ ፍሰት ማስተካከያ ሥራ ካከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል ከብሔረጽጌ – ቀይመስቀል መሄጃ፣ ቃሊቲ ገነት መናፈሻ ኮንዶሚኒየም፣ በተለምዶ ፍየል ቤት በሚባለው አካባቢ እና ጎሮ ድልድይ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

የጎርፍ አደጋ ስጋትን አስቀድሞ ለመከላከል ባለሥልጣን መስሪያቤቱ በበጋው ወራት መጠነ ሰፊ የድሬኔጅ መስመር ፅዳትና ጥገና ሥራ ሲያከናውን የቆየ ሲሆን፣ በ2015 በጀት ዓመት ብቻ 403 ኪሎ ሜትር ርቅት የሚሸፍን የድሬኔጅ መስመር ፅዳትና ጥገና ማከናወኑ ይታወሳል፡፡

መንገድ የሁሉም ህብረተሰብ ክፍል የጋራ መጠቀሚያ ሀብት መሆኑን በመገንዘብ መላው የከተማችን ነዋሪ በመንገድ አካላት ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ህገ-ወጦችን በጋራ እንዲከላከል ባለሥልጣን መስሪያቤቱ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.