ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለም/ቤት ካቀረቡት ሪፖርት /በበጀት አመቱ ከመንገድ ልማት አንፃር የተከናወኑ ተግባራት/
የከተማውን የመንገድ መረብ ሽፋን የሚያሳድጉ፣ የትራፊክ ፍሰቱን የሚያሳልጡ፣ የመንገድ ድህንነቱን የሚያረጋግጡ፣ ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩ፣ የጉዞ ጊዜን እና ገንዘብን የሚቀንሱ የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ስራዎች ተከናውነዋል፤
በበጀት አመቱ በአጠቃላይ 188.83 ኪ.ሜ. የአስፋልት፣ የጠጠር፣ የኮብልስቶን፣ የእግረኛ መንገድ፣ የድሬኔጅ እና ድጋፍ ግንብ ስራዎች መከናወን ችሏል፤
በበጀት እጥረት እና አበዳሪ ድርጅቶች ቃል የጉቡትን ክፍያ በማቆማቸው ምክንያት በህብረተሰቡ ዘንድ በከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ችግር ፈጥሮ የነበረው የቃሊቲ ቱሉ ዲምቱ እና የቃሊቲ – ቂሊንጦ የመንገድ ስራ ፕሮጀክቶች የከተማ አስተዳደሩ በልዩ ሁኔታ በሰጠው ውሳኔ መሰረት በራስ በጀት ግንባታቸው ቀጥሎ እና በከፍተኛ ፍጥነት እየተከናወኑ በመሆኑና የግራ ክንፍ ለአገልግሎት ክፍት መደረግ መቻሉ የህዝቡ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ምላሽ አግኝቷል፤
በአሁኑ ወቅት ካሉን የመንገድ ፕሮጀክቶች ውስጥ ከ2,300 ሜትር በላይ ርዝመት ያላቸው ግዙፍ ተሸጋጋሪ እና የወንዝ መሻገሪያ ድልድዮችን እየተገነቡ ይገኛሉ፤
የድልድዮቹ ግንባታ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ በቀለበት መንገድ ባሉ የመንገድ መጋጠሚያዎች ላይ የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት በቦሌ ሚካኤል፣ በኢምፔሪያል እና በለቡ የመንገድ መጋጠሚያዎች ላይ እየተገነቡ የሚገኙት ሦስት የትራፊክ ማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድዮች ግንባታ ወደ በመጠናቀቅ ላይ ሲሆኑ በከፊል አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል፤
የጥገና ስራን በተመለከተ በአጠቃላይ 822.99 ኪ.ሜ የአስፋልት መንገድ፣ የጠጠር፣ የእግረኛና የከርቭስቶን መንገድ፣ የድሬኔጅ መስመሮች ጽዳት እና ጥገና፣ የእግረኛ መከላከያ እንዲሁም የመንገድ ቀለም ቅብ ስራ ተከናውኗል፤