ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለም/ቤት ካቀረቡት ሪፖርት /በበጀት አመቱ የኘሮጀክቶች አፈፃፀምን በተመለከተ በከተማ አስተዳደሩ የተከናወኑ ተግባራት/
የህዝቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች መመለስ ላይ ጉልህ ሚና ያላቸው አዳዲስና ከባለፈው በጀት አመት የተሻገሩ ኘሮጀክቶችን ከ6ዐ ቢሊየን ብር በላይ በጀት በመመደብ በጊዜ የለንም መንፈስ፣ ወጪ ቆጣቢና ቶሎ ለአገልግሎት ለማብቃት በሚያስችል ፍጥነትና ጥራት እየገነቡ ይገኛሉ፤
በዝርዝር ለመመልከት፡-
=> 538 የመንገድና ተያያዥ ኘሮጀክቶች፣
=> 264 የውሃና ፍሳሽ ኘሮጀክቶች፣
=> 39 የጤና ፕሮጀክቶች፣
=> 1ዐ7 የትምህርት ፕሮጀክቶች፣
=> 99 የሼዶች፣
=> 9 የአረንጓዴና የፓርክ ኘሮጀክቶች፣
=> 28 የእስፖርት ማዘወተሪያ እና የወጣቶች ስብዕና መገንቢያዎች፣
=> 258 ልዩ ልዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው ኘሮጀክቶች፣
=> ከ1ዐ,ዐዐዐ በላይ መኖሪያ ቤቶች፣
=> በጥቅሉ በከተማው በጀት 11,3ዐ7 ኘሮጀክቶች እየተገነቡ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 5,256 ኘሮጀክቶችን ማጠናቀቅ የተቻለ ሲሆን፣ ይህ ቁጥር በህብረተሰብ ተሳትፎ የተሰሩትን አይጨምርም፡፡
——–
የነባር ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ አፈፃፀምን በተመለከተ:-
=> አድዋ ሙዚየም ዜሮ ኪ.ሜ ፕሮጀክት ግንባታ ከነበረበት 74.78% ወደ (86%)፣ ማድረስጠተችሏል፤
=> የትራንስፖርት ቢሮ ተቋማት ህንፃ ግንባታን ከነበረበት 45.79% ወደ (61.5%) ማድረስ ተችሏል፤
=> የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ግንባታ ከነበረበት 43% ወደ (71.2%) ማድረስ ተችሏል
=> እንዲሁም የየካ 2 መኪና ማቆሚያ ግንባታ ፕሮጀክት ግንባታ ከነበረበት 24.27% ወደ (48.2%) ማድረስ ተችሏል፤
=> አዲስ አፍሪካ ኢግዚቪሽን ማዕከል ከነበረበት 6ዐ% ወደ (80%) ማድረስጠተችሏል፤
=> የአቃቂ አለምአቀፍ እስቴዲየም ከነበረበት 65% ወደ 8ዐ% ማድረስ ተችሏል፤
———
የአዳዲስ የፕሮጀክቶች ግንባታ አፈፃፀምን በተመለከተ:-
=> አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪ ክላስተር ግንባታ ሎት አንድ (16%) እና ሎት ሁለት (46%) ማድረስ ተችሏል
=> የግብርና ምርቶች የገበያ ማዕከላት ማለትም ለሚኩራ ሳይት አንድ (74%)፣ለሚኩራ ሰሚት ሳይት (32%) ኮልፌ ቤቴል ሳይት (88%) እና የላፍቶ ምዕራፍ 86% ላይ ለማድረስ ተችልሏ፤
=> አቃቂና የግብርና ምርት እና የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች የገበያ ማዕከል ፕሮጀክት ተጠናቋል፡፡
=> የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ግንባታ (20%) ማድረስ ተችሏል
=> ቤተል መንዲዳ ሆስፒታል ፕሮጀክት ግንባታ 52% ማድረስ ተችሏል፤
=> ላፍቶ ሆስፒታል ፕሮጀክት ግንባታ 36% ማድረስ ተችሏል
=> የጥሩነሽ ቤጂንግ ማስፋፍያ ፕሮጀክት ግንባታ 37% ማድረስ ተችሏል፡፡