የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በከንቲባ አዳነች አቤቤ የቀረበውን የአዲስ አበባ ከተማ የ2015 በጀት አመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል::
ምክር ቤቱ በ2ኛ ዓመት በ4ኛ መደበኛ ጉባዔው የከተማ አስተዳደሩን የ2015 በጀት አመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
ከአገልግሎት አሰጣጥና ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለማስተካከል ከተማ አስተዳደሩ የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ እንዲቀጥል የምክር ቤት አባላት አሳስበዋል፡፡ የከተማዋን ሰላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ ሕዝቡን ያሳተፉ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለበትም አባላቱ አሳስበዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማ አስተዳደሩ የህዝቡን የኑሮ ጫና የሚያቀሉ እና የኑሮ ውድነቱን መቋቋም ለሚያስችሉ ስራዎች የተለየ ትኩረት ሰጥቶ በቀጣዩ በጀት አመት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡