+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የመቃረቢያ መንገዶች ግንባታ እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በጠጠር ደረጃ የመቃረቢያ መንገዶችን በመገንባት የመንገድ መሠረተ ልማትን ተደራሽ የማድረግ ተግባሩን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ባለሥልጣን መስሪያቤቱ በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ከሚያከናውናቸው የአስፋልት ኮንክሪትና የኮብል መንገዶች ግንባታ በተጨማሪ የመንገድ መሰረተ-ልማት ባልተዳረሰባቸው አካባቢዎች የጠጠር መንገዶችን በመገንባት ለአገልግሎት እያበቃ ይገኛል፡፡

አሁን ላይ ከ283,626 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በቦሌ፣ በለሚ ኩራ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ እና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች 39 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍኑ የመቃረቢያ መንገዶችን እየገነባ ይገኛል፡፡

በግንባታ ላይ የሚገኙት እነዚህ የጠጠር መቃረቢያ መንገዶች በየአካባቢው ያለውን የመንገድ መሠረተ ልማት ችግር ከመፍታት ባሻገር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ይኖራቸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.