+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በተለያዩ ምክንያቶች ጉዳት የደረሰባቸው የውስጥ ለውስጥ የኮብልስቶን መንገዶችን እየተጠገኑ ነው

አዲስ አበባ፡ ሰኔ 29 ቀን 2015 ፣-የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በከተማዋ በተለያዩ አከባቢዎች በጎርፍ እና በከባድ ተሸከርካሪዎች ጉዳት የደረሰባቸውን የውስጥ ለውስጥ የኮብል ስቶን መንገዶች በመጠገን ላይ ይገኛል፡፡

ባለሥልጣን መስሪያቤቱ 69 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የኮብል መንገዶች ጥገና በበጋው ወራት አከናውኗል፡፡

አሁን ላይ የጥገና ስራ ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል ለሚ ኩራ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው ለገጂላ ሰፈር፣ ለሚ ኩራ ወረዳ 13 ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስትያን፣ የካ ወረዳ 12 ኮተቤ ዩኒቨርሲቲ ጀርባ፣ አቃቂ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ገላን ኮንዶሚኒየም፣ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ቄራ ከብት በረት እና ጀሞ 3 ታፍ ማድያ አከባቢ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.