የውጨኛው ቀለበት መንገድ አካል በሆነው የጎሮ አደባባይ – አይ.ሲ.ቲ ፓርክ ጎዳና ላይ አስፋልት መንገድ እየተጠገነ ነው
ሰኔ 19 ቀን 2015 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፡- የቱሉ ዲምቱ የፍጥነት መንገድን ከሰሜን ምስራቅ የአዲስ አበባ አካባቢዎች ጋር በአጭር ርቀት የሚያገናኘው እና በየዕለቱ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ትራፊክ የሚያስተናግደው ከጎሮ አደባባይ – አይሲቲ ፓርክ የአስፋልት መንገድ የጥገና ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡
የከተማዋ ሌላኛው የመግቢያና መውጪያ ዋነኛ ኮሪደር በሆነው የቱሉ ዲምቱ – ጎሮ አደባባይ ዋና መንገድ ላይ ከዚህ ቀደም 3.1 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የመንገዱ ክፍል መጠገኑ ይታወሳል፡፡
አሁን ላይ ባለስልጣን መስሪያቤቱ 1.5 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና በ10 ሜትር የጐን ስፋት የአስፋልት ጥገና ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰትና ጫና ያለባቸውን መንገዶች በጥናት በመለየት ለትራፊክ ፍሰቱ ምቹና የተሳለጠ እንዲሆን ሁሉን አቀፍ የጥገና ስራዎች እያከናወኑን እንደቀጠለ ነው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity