+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ ስራዎች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የመንገድ መሰረተ ልማት ተደራሽነትን ለማሳደግ በተለያዩ ማዕዘናት በተገነቡ የ40/60 እና 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡

ከዚህ ቀደም ምንም ዓይነት የመንገድ መሰረት ልማት ባልነበራቸው የኮዬ ፈቼ የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ በተለያዩ የስራ ተቋራጮች በመገንባት ላይ የሚገኙት የመንገድ ፕሮጀክቶች አምስት ናቸው፡፡

ከእነዚህ ፕሮጀክቶች መካካል ከ385 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ የግንባታ ዋጋ እየተከናወነ የሚገኘው ፕሮጀክት 18 የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ አንዱ ነው፡፡

አይ.ኤፍ.ኤች ኢንጂነርስ በተባለው የስራ ተቋራጭ የተገነባው የፕሮጀክት 18 መንገድ በአጠቃላይ 8.2 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና ከ10 እስከ 40 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሲሆን አሁን ላይ የግንባታ ሥራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል፡፡

የኮዬ ፈቼ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የመንገድ ግንባታ አካል የሆነው የፕሮጀክት 18 መንገድ 6.4 ኪሎ ሜትር በአስፋልት እና 1.8 ኪሎ ሜትር ደግሞ በኮብል የተገነባ ነው፡፡

በሌላም በኩል የኮዬ ፈቼ ኮንዶሚኒየም ፕሮጀክት 11 እና ሎት 1 ኮንዶሚኒየም የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ፣ የአስኮ፣ የኤምፔሪያል እና የቡልቡላ ኮንዶሚኒየም የመንገድ ግንባታ ሥራን እስከ በጀት ዓመቱ ማጠናቀቂያ ድረስ ሙሉ በሙሉ ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

በተጨማሪም የቦሌ አያት 1፣ 2፣ 3 እና 4 እንዲሁም የአያት መሪ ሳይት 4 እና የበሻሌ ኮንዶሚኒየም የአስፋልት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.