+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በቀን እስከ 80 ሺ ተሽከርካሪዎችን የማስተናገድ አቅም ያለው የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ በቅርቡ ይጠናቀቃል

አዲስ አበባ፣ሰኔ 13 ቀን 2015 ዓ.ም፡- በአዲስ አበባ ከተማ በቀን እስከ 80 ሺ ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ እንዲችል ተደርጎ ከፍ ባለ የጥራት ደረጃ እየተገነባ የሚገኘው የኤምፔሪያል ማሳለጫ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ በቅርቡ ተጠናቆ ሙሉ ለሙሉ ለትራፊክ ክፍት ይደረጋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የማሳለጫ ድልድዩ የመቃረቢያ መንገዶች እና ቀሪ የግንባታ ቦታዎች ላይ የአስፋልት ማንጠፍ ስራዎች እየተከናወኑ ሲሆን አጠቃላይ የፊዚካል አፈፃፀሙም 82 በመቶ ላይ መድረስ ችሏል፡፡

በቀጣይ ጥቂት ቀናት ውስጥ ከመንገድ ዳር መብራት ተከላ እና ከእግረኛ መንገድ ስራዎች ውጪ የአስፋልት ማንጠፍ ስራው ተጠናቆ በሙሉ አቅም ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡

ይህ የመንገድ ፕሮጀክት በቻይናው ፈርስት ሀይ ዌይ ኢንጂነሪንግ እየተገነባ የሚገኝ ሲሆን የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ስታዲያ እና G&Y ኢንጂነሪንግ የተባሉ አማካሪ ድርጅቶች በጋራ እየተከታተሉት ይገኛሉ፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ ከማሳለጫ ድልድዩ በተጨማሪ የመቃረቢያ መንገዶቹን ጨምሮ አጠቃላይ 1.8 ኪ.ሜ ርዝመትና 40 ሜትር የሚደርስ የጎን ስፋት ያለው ሲሆን ለግንባታ ወጪውም ከ714.8 ሚሊዮን ብር በላይ ተይዞለታል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.