በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የኮብልስቶን መንገድ ግንባታና ጥገና ስራ በመከናወን ላይ ነው
አዲስ አበባ፡ ሰኔ 9 ቀን 2015 ፣- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የከተማዋን የመንገድ ሽፋን ለማሳደግ ከአስፋልት መንገድ ግንባታ ጎን ለጎን የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በኮብልስቶን በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡
ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ባለፉት 11 ወራት 60 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የኮብልስቶን መንገድ የግንባታ እና 25 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የኮብል ስቶን መንገድ የጥገና ስራ ማከናወኑን የባለስልጣኑ የኮብልስቶን ፕሮጀክት ስራ አስክያጅ ኢንጅነር ብስራተገብርኤል አሰፋ ገልጸዋል ፡፡
ሥራ አስኪያጁ አያይዘውም ቀደም ሲል ተገንብተው በተለያየ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው የኮብልስቶን መንገዶች እየተጠገኑ መሆኑን ጠቁመው፣ አሁን ላይ 25 ኪሎ ሜትር የውስጥ ለውስጥ የኮብል ስቶን መንገድ ጥገና ስራ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
የኮብል ስቶን መንገድ ግንባታ እየተከናወነባቸው ከሚገኙ አካባቢዎች መካከል ቱሉ ዲምቲ ከጎመጁ ነዳጅ ማደያ ጀርባ እና ጀሞ መስታዎት ፋብሪካ ያሉ አካባቢዎች ተጠቃሾ ናቸው።
በኮብል ስቶን ደረጃ እየተገነቡ የሚገኙት የውስጥ ለውስጥ የመንገዶች የሥራ እንቅስቃሴ በባለሥልጣኑ የስራ ኃላፊዎች፣ በወረዳው የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበርያ ጽ/ቤት እንዲሁም ከአካባቢው የልማት ኮሚቴ አባላት በጋራ ጎብኝተዋል፡፡
የመንገድ መሰረተ ልማት ተደራሽነትን ለማሳደግ በመንግስት በኩል ከሚደረገው ጥረት ባሻገርም በውስጥ ለውስጥ የኮብል ስቶን መንገዶች ግንባታ የህብረተሰቡ የልማት ተሳትፎ ይበልጥ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የጉብኝቱ ተሳታፊዎች ጠቁመዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity