የቀራንዮ ድልድይ ግንባታ በመልካም አፈፃፀም ላይ ይገኛል
አዲስ አበባ ሰኔ 8 ቀን 2015 ፣- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ውስጥ እየገነባቸው ከሚገኙ የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነውን ቀራንዮ ድልድይ የግንባታ በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እየሰራ ይገኛል፡፡
የፕሮጀክቱ ዋነኛ ዓላማ የመንዲዳ እና የሺ ደበሌ አካባቢዎችን ከውስጠኛው የቀለበት መንገድ ምዕራባዊ ክፍል ጋር በማስተሳሰር የአካባቢውን የትራፍክ ፍሰት ለማቀላጠፍ ነው፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በራስ ኃይል እየገነባው የሚገኘው የቀራንዮ ድልድይ ግንባታ ፕሮጀክት 8 ሜትር ርዝመት እና 16 ሜትር የጎን ስፋት እንዲሁም 13 ሜትር ከፍታ አለው፡፡
አሁን ላይ የድልድዩ ድጋፍ ግንብ ሥራ ተጠናቆ የኮንክሪት ሙሌት ለመከናወን ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡
የድልድዩ ግንባታ ስራ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሲደረግ ሆላንድ ኤምባሲ ወደ የሺ ደበሌ እና መንዲዳ አካባቢ መሄድ ለሚፈልጉ ተሽከርካሪዎች አቋራጭ መንገድ ሆኖ ያገለግላል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity