ከደጃች ውቤ ወደ ሶር አምባ ሆቴል የሚያቋርጠው መንገድ የጥገና ስራ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ሆነ
ሰኔ 6 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከደጃች ውቤ ወደ ሶር አምባ ሆቴል አቅጣጫ የሚወስደውን አቋራጭ የአስፋልት መንገድ በመጠገን ለትራፊክ ክፍት አደርጓል፡፡
በተለያየ ምክንያት የተጎዳውን የአስፋልት ክፍል ለይቶ በማንሳት 264 ሜትር ርዝመት በ7 ሜትር የጎን ስፋት የአስፋልት ጥገና የተከናወነለት ይህ የመንገድ ክፍል በአካባቢው ያለውን የትራፊክ ፍሰት በማሻሻል የተቀላጠፈ የትራፊፈክ ፍሰት እንዲኖር ያግዛል፡፡
በዚህ ዓመት ከበልግ ወቅት ጀምሮ እስከ አሁን የዘለቀው የዝናብ ሁኔታ በባለሥልጣኑ አጠቃላይ የመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራዎች ላይ ተፅእኖ እያሳደረ ቢሆንም የአየር ሁኔታ አመቺነትን በመጠቀም በበጀት ዓመቱ በዕቅድ የተያዙ ሥራዎችን ለማሳካት በትጋት እየተሰራ ይገኛል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity