+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ከአደጋ የፀዳ የትራፊክ እንቅስቃሴ እንዲኖር እየተሰሩ የሚገኙ የመንገድ ዘርፍ ሥራዎች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1 ቀን 2015ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በመንገድ ጥገና መስክ ከሚያከናውናቸው ሥራዎች መካከል የመንገድ ጠርዝና አካፋይ፣ እንዲሁም የእግረኛ መከላከያ አጥር ጥገና እና ቀለም ቅብ ሥራዎች ይገኙበታል፡፡

ባለሥልጣን መስሪያቤቱ በመዲናዋ ከአደጋ የፀዳ የትራፊክ እንቅስቃሴ እንዲኖር ለማስቻል ባለፉት አስር ወራት ብቻ 3 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍን የእግረኛ መከላከያ አጥር ጥገና እና 125 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የቀለም ቅብ ስራ አከናውኗል፡፡

በመንገድ ጥገና መስክ እየተከናወነ የሚገኘው የመንገድ ጠርዝና አካፋይ የቀለም ቅብ ሥራ የትራፊክ አደጋ እንዲቀንስ ከሚያበረክተው አስተዋፅኦ ባሻገር ለከተማችን ጎዳናዎች ተጨማሪ ውበት የሚያጎናፅፍ ነው፡፡

የመንገድ ሀብታችንን እንንከባከብ፣ በጋራ እንጠብቅ፣ በአግባቡ እንጠቀም!

ሠናይ ቀን!

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.