ከጎተራ ወደ አደይአበባ የሚወስደው የአስፋልት መንገድ የጥገና ስራ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ሆኗል፡፡
ግንቦት 30 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከጎተራ በቡና ቦርድ ወደ አደይ አበባ የሚወስደውን አቋራጭ የአስፋልት መንገድ ጥገና ስራ አጠናቆ ለትራፊክ ክፍት አድርጓል፡፡
ይህ አቋራጭ መንገድ ከባድ ተሸከርካሪዎችን ጨምሮ ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት የሚያስተናግድ በመሆኑ የነበረው የመንገድ ጉዳት የትራፊክ እንቅስቃሴውን አስቸጋሪ አድርጎት ቆይቷል፡፡
አሁን ላይ የተጎዳውን የአስፋልት ክፍል ለይቶ በማንሳት 100 ሜትር ርዝመት በ8 ሜትር የጐን ስፋት የሸፈነ የጥገና ስራ ተከናውኖ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
በተመሳሳይም በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ጉዳት የደረሰባቸውን የአስፋልት መንገዶች በመለየት የጥገና ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡
ሰሞኑን የመንገድ ጥገና ስራ እየተከናወነባቸው ከሚገኙ አካባቢዎች መካከል ከመገናኛ አያት፣ ከጥቁር አንበሳ – ለገሀር፣ እሪ በከንቱ አካባቢ፣ ከኮካኮላ- መሳለሚ እንዲሁም ከአውቶብስ ተራ – ፖስተር ያሉት ጎዳናዎች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity