+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በተለያዩ ምክንያቶች ለብልሽት የተዳረጉ የማንሆል ክዳኖችን በአዲስ የመተካት ስራ በመከናወን ላይ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በከተማዋ ጎዳናዎች የድሬኔጅ መስመር ላይ የሚገኙና በልዩ ልዩ ምክንያቶች የተጎዱና ክፍት የሆኑ የውሃ መፋሰሻ መስመር ክዳኖችን በአዲስ እየተካ ይገኛል፡፡

የማንሆል ክዳንኖች የመቀየር ስራ እያከናወነ ከሚገኝባቸው አካባቢዎች መካከል ከአየር ጤና – አንፎ፣ ቻይና ካምፕ አካባቢ፣ ከመድኃኒአለም – ዊንጌት እና ኳስ ሜዳ አካባቢ እንዲሁም በሌሎች የከተማዋ አካባቢዎች ይገኙበታል፡፡

በቀጣይም በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች ጉዳት የደረሰባቸውን ክፍት የማንሆል ክዳኖች የመጠገንና የመቀየር ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

በከተማዋ መንገዶች ላይ በማንሆል ክዳን አገልግሎት የሚያቀርቡ ሌሎች መሰረት-ልማት አቅራቢ ተቋማትም ክፍት የማንሆል ክዳኖችን ተከታትለው በመክደን ለህብረተሰቡ እንቅስቃሴ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጥሩ ባለሥልጣኑ በዚሁ አጋጣሚ መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡

ሕብረተሰቡም የጋራ መጠቀሚያ ሀብት የሆነውን የመንገድ መሰረተ ልማት በባለቤትነት ስሜት በመጠበቅ፣ በመንከባከብና በአግብቡ በመጠቀም ለመንገድ ሀብቱ ደህንነት አውንታዊ አበርክቶውን እንዲወጣ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads

Comments are closed.