+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የአስፋልት ጥገና ስራ ከዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታል ወደ ቃኘው 05 አደባባይ በመከናወን ላይ ነው

ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታል ወደ ቃኘው 05 አደባባይ የሚያወጣውን የውስጥ ለውስጥ የአስፋልት መንገድ የጥገና ስራ እያከናወነ ነው፡፡

በማዕከላዊ አዲስ አበባ የመንገድ ሀብት አስተዳደር ስር የጥገና ስራው በመከናወን ላይ የሚገኘው ይህ የመንገድ የጥገና ስራ የተጎዳውን የአስፋልት ክፍል በማንሳትና መንገዱን ከነበረበት በማስፋት ደረጃውን በጠበቀ መልኩ 550 ሜትር ርዝመት በ9 ሜትር የጐን ስፋት እየተከናወነ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም የጥገና ስራው 670 ሜትር ርዝመት ያለው የድሬኔጅ መስመር ዝርጋታን ያካተተ ነው፡፡

ይህ መንገድ ከዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታል ወደ ፈረንሳይ እና ቤላ ለሚሄዱ ተሽከርካሪዎች በአቋራጭነት የሚያገለግል በመሆኑ የጥገና ስራው መከናወኑ በአካባቢው የሚኖረውን የትራፊክ እንቅስቃሴ የተሳለጠ ያደርገዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.