+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የቦሌ ሚካኤል ተሸጋጋሪ ድልድይ ግንባታ አሁናዊ ሁኔታ

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የከተማዋን የትራፊክ ፍሰት የሚያሻሽሉ 6 የትራፊክ ማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድዮችን በተለያዩ አካባቢዎች በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡

አሁኑ ላይ በከተማዋ የትራፊክ ማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድይ እየተገነባባቸው ከሚገኙ ስፍራዎች መካከል የቦሌ ሚካኤል የመንገድ መጋጠሚያ አንዱ ነው፡፡

በዚህ ሥፍራ ቀደም ሲል የነበረውን የትራፊክ ፍሰት ለማሻሻል በቦታው ላይ የነበረውን አደባባይ በማንሳትና በትራፊክ መብራት በመተካት ችግሩን ለመፍታት ጥረት ተደርጓል፡፡

ይሁን እንጂ ቀለበት መንገዱ የሚያስተናግደው የትራፊክ እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጨመሩና በቦሌ ቡልቡላ አካባቢም የከተማዋ እድገት እየተፋጠነ በመምጣቱ በቦሌ ሚካኤል የመንገድ መጋጠሚያ ላይ የትራፊክ ፍሰቱን በዘላቂነት ማሻሻል የሚያስችል መፍትሄ መሻት ግድ ብሏል፡፡

በመሆኑም እየለማ በመጣው የቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ከተገነቡ አዳዲስ መንገዶች ጋር ተሳስሮ ከሳሪስ አቦ ወደ ቦሌ አቅጣጫ ከሚወስደው የቀለበት መንገድ ጋር በተለያዩ መጋጠሚያዎች የሚያገናኙ የመቃረቢያ መንገዶችን ጨምሮ የቦሌ ሚካኤል የትራፊክ ማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድይ ፕሮጀክት ግንባታ እውን እንዲሆን ምክንያት ሆኗል፡፡

ይህ የመንገድ ግንባታ ፕሮጄክት የመቃረቢያ መንገዶችን ጨምሮ በአጠቃላይ 4 ነጥብ 55 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 30 ሜትር የጎን ስፋት አለው፡፡ ፕሮጅክቱ ከ720 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ አሰር ኮንስትራክሽን የተባለ የሀገር ውስጥ የሥራ ተቋራጭ እየገነባው የሚገኝ ሲሆን፣ የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ደግሞ በሀይ ዌይ ኢንጂነርስ አማካሪ ኩባንያ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ቀደም ሲል 600 ሜትር ርዝመት ያለው የቦሌ ሚካኤል ትራፊክ ማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድይ ግንባታ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት የተደረገ ሲሆን፣ ከአጠቃላይ የመንገድ ፕሮጀክቱ ክፍል 3.8 ኪሎ ሜትሩ የመጀመርያ አስፋልት ደረጃ የለበሰ ከመሆኑም በተጨማሪ በቀሪው 200 ሜትር በሚሆነው የመንገዱ ክፍል የአስፋልት ንጣፍ ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

አሁን ላይ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ የፊዚካል አፈፃፀም 83 በመቶ ላይ የደረሰ ሲሆን፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ በመሰራት ላይ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.