የቃሊቲ – ቱሉ ዲምቱ የመንገድ ግንባታ ኘሮጀክት የግራ ክፍልን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ እየተሰራ ነው
ግንቦት 28 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከቃሊቲ ቀለበት መንገድ አደባባይ – ቱሉ ዲምቱ አደባባይ ያለውን የመንገድ ግንባታ ቀሪ ክፍል በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡
የመንገድ ግንባታ ስራው አጠቃላይ 11 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 50 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሲሆን፣ ግንባታው ሶስት ዋና ዋና ማሳለጫዎችን ያካተተ ነው፡፡
ከዚህ ቀደም የመንገዱ ቀኝ መስመር የመጀመሪያ ደረጃ አስፋልት ለብሶ ለትራፊክ ክፍት የተደረገ ሲሆን፣ አሁን ላይ የመንገድ ፕሮጀክቱ ግራ መስመር 8.5 ኪሎ ሜትር የሚሆነው የመጀመሪያ ደረጃ የአስፋልት ንጣፍ ስራ ተከናውኗል፡፡ ቀሪው 2.5 ኪሎ ሜትር እና ከሳሪስ ወደ ቃሊቲ ቀለበት መንገድ አደባባይ መግቢያ መንገድ በአጭር ጊዜ ውስጥ የአስፋልት ማልበስ ስራ በማከናወን ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል፡፡
የአስፋልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ስራውን የቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ (cccc) በተባለ ሥራ ተቋራጭ እየተገነባ ሲሆን፣ የፕሮጀክቱን ማማከርና ቁጥጥር ስራ ደግሞ ኢንጂነር ዘውዴ እስክንድር አማካሪ ድርጅት እየተከታተለው ይገኛል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity