+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ከአደይ አበባ ስቴዲየም ወደ ቦሌ ቀለበት መንገድ የሚወስድ የመቃረቢያ መንገድ ግንባታ እየተከናወነ ነው

ግንቦት 19 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከአደይ አበባ ስታዲየም ወደ ቦሌ ቀለበት መንገድ የመወስደውን ነባር መንገድ በጠጠር ደረጃ የማስፋፊያ ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡

ከዚህ ቀደም አገልግሎት ይሰጥ የነበረው መንገድ ጠባብና ረጅም ጊዜ አገልግሎት የሰጠ በመሆኑ በአካባቢው የነበረውን የትራፊክ እንቅስቃሴ አስቸጋሪ አድርጎት ቆይቷል፡፡

አሁን ላይ ያለውን የትራፊክ ፍሰት ታሳቢ በማድረግ በ15 ሜትር የጐን ስፋት 1.4 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የመዳረሻ መንገድ ግንባታ ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

የመንገድ ግንባታ ስራው ሲጠናቀቅ የአካባቢውን ህብረተሰቡ የመግቢያና መውጪያ ችግር የሚፈታ ከመሆኑም በተጨማሪ በቅርቡ የግንባታ ስራው ለሚጀመረውና ከመድኃኒዓለም አደባባይ – እንግሊዝ ኤምባሲ ለሚወስደው መንገድ እንደ አማራጭነት መንገድ በመሆን የሚያገለግል ይሆናል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በአዳዲስ የመኖሪያ አካባቢዎች በጠጠር ደረጃ መንገዶችን በመገንባት ለሕብረተሰቡ የአክሰስ መንገዶች ተደራሽ ከማድረጉም በተጨማሪ ከዋና መንገዶች ጋር በቀላሉ ሊያገናኙ የሚያስችሉ አጫጭርና አቋራጭ የጠጠር መንገዶችን በስፋት እየገነባ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.