+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የአቋራጭ መንገዶች የአስፋልት ጥገና ሥራ እንደቀጠለ ነው

ግንቦት 18 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የከተማዋን የትራፊክ እንቅስቃሴ ምቹና ቀልጣፋ ለማድረግ በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች የመንገድ ጥገና ሥራዎች በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

በዚህ ሳምንት በማዕከላዊ አዲስ አበባ ሪጅን የአስፋልት ጥገና እየተካሄደባቸው ከሚገኙ አካባቢዎች አንዱ በተለምዶ ዶሮ ማነቂያ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ወደ ሲኒማ አምፒር የሚወስደው የመንገድ ክፍል ይገኝበታል፡፡

ይህ አቋራጭ መንገድ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት በመስጠቱ የተጎዳና ለአሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ አስቸጋሪሆኖ ቆይቷል፡፡ በመሆኑም የተጐዳውን አስፋልት በማንሳት የጥገና ስራው እየተከናወነ ሲሆን፣ አጠቃላይ የጥገና ስራው 795 ሜትር ርዝመት እና በአማካይ በ7 ሜትር የጎን ስፋት የሚሸፍን ነው፡፡

የመንገዱ መጠገን በአካባቢው የሚኖረውን የትራፊክ እንቅስቃሴ ከማቀላጠፉም ባሻገር የአካባቢውን ገፅታ በመቀየር ተጨማሪ ውበት የሚያላብስ ይሆናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.