+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በመንገዶች ላይ የሚከሰተውን የጐርፍ አደጋ ስጋት ለመከላከል በተለያዩ አካባቢዎች የሚካሄደው የግንባታና ጥገና ስራ እንደቀጠለ ነው

ግንቦት 11 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በዝናብ ወቅት በመንገዶች ላይ የሚከሰተውን የጎርፍ አደጋ ስጋት ለመከላከል በበጀት ዓመቱ 10 ወራት 340 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የድሬኔጅ መስመር ፅዳትና ጥገና ሥራ አከነዋውኗል፡፡

በከተማዋ ለጎርፍ አደጋ ስጋት ተጋላጭ ናቸው ተብለው በተለዩ አካባቢዎች ላይም እንደ ችግሮቹ ባህሪ የተለያዩ መፍትሄዎችን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

ባለሥልጣን መስሪያቤቱ በዕቅድ ይዞ እየሠራቸው ከሚገኙ የጎርፍ አደጋ ስጋት ቅድመ መከላከል ሥራዎች በተጨማሪ የበልግ ወቅት የዝናብ መራዘሙን ተከትሎ ከህብረተሰቡ የመጡ ጥቆማዎችን መሰረት በማድረግ ፈጣን የማስተካከያ እርምጃዎች እየወሰደ ይገኛል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት ፈጣን ምላሽ ከተሰጣቸው አካባቢዎች መካከል ቦሌ ክፍለ ከተማ ጀርባ፣ ኳስ ሜዳ፣ ቦሌ ሆምስ ገነት ጨፌ አካባቢ፣ መሪ 40/60 ቡኬ ወንዝ አካባቢ፣ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አካባቢ፣ ሽሮ ሜዳ መካነ እየሱስ ቤተ-ክርስቲያን እንዲሁም ግሩም ሆስፒታል አካባቢ ተጠቃሾች ናቸው፡፡

በዝናብ ወቅት በመንገድ ላይ ለሚከሰተው ጎርፍ ዋነኛ ምክንያት ተብለው ከተለዩ ችግሮች መካከል ጠጣር ቆሻሻዎችን በመንገድ ዳር የውሃ መፋሰሻ መስመሮች ላይ መጣል፣ በድልድዮች እና በወንዝ ዳርቻዎች የግንባታ ተረፈ ምርትና አፈር መድፋት፤ እንዲሁም በእርሻ ሥራ እንቅስቃሴ ሳቢያ የወንዞችን ተፈጥሯዊ ፍሰት የሚያስተጓጉሉ ተግባራት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

በመሆኑም ህብረተሰቡ የቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓቱን በማዘመን፣ የድሬኔጅ መስመሮችን ከጉዳት በመጠበቅና በመንገድ ሃብት ላይ ህገወጥ ተግባር የሚፈፀሙ አካላትን በመከላከል የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ ባለስልጣን መስሪያቤቱ መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.