“የቆሻሻ አወጋገድ ባህላችንን በማዘመን ፅዱ የሆኑ የዝናብ ውሃ መፍሰሻ መስመሮች እንፍጠር።”
በመዲናችን ጎርፍ እንዲከሰት ከሚያደርጉ ዋነኛ ምክንያቾች መካከል የውሃ መፍሰሻ መስመሮች ውስጥ የሚጣሉ ሊበሰብሱ የማይችሉ የፕላስቲክ የውሃ መጠጫ ዕቃዎች፣ ፌስታሎች እና መሰል የፕላስቲክ እቃዎች እንዲሁም በመንገድ ዳር የውሃ መፋሰሻ መስመሮች ፣ በወንዞች ዳቻ እና ድልድዮች ስር የሚደፋ ቆሻሻ እና የግንባታ ተረፈ ምርት የሚጠቀሱ ናቸው። “ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ” ነው እና ብሂሉ የዝናብ ውሃ መፍሰሻ መስመሮች ለታለመላቸው ዓላማ ብቻ እንዲውሉ የበኩላችንን ኃላፊነት በመወጣት በከተማችን የሚከሰት የጎርፍ አደጋን እንቀንስ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የዘወትር መልዕክት ነው።
መልካም ቀን!