የጎርፍ አደጋ ስጋትን ለመከላከል ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ በሚወስደው ጎዳና ላይ የድሬኔጅ መስመር ግንባታ ስራ ተከናወነ
ግንቦት 8 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በዝናብ ወቅት ለጎርፍ ተጋለጭ የሆኑ ቦታዎችን በመለየት የቅድመ መከላከል የግንባታ፣ ጥገና እና የፅዳት ስራዎች እያከናወነ ይገኛል፡፡
ባለስልጣኑ የጎርፍ ስጋት አለባቸው ብሎ ከለያቸው አካባቢዎች መከላከል በተለምዶ ግሎባል ሆቴል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የቀላል ባቡር መስመርን ተከትሎ ይከሰት የነበረውን የጎርፍ ችግር ለመቅረፍ የድሬኔጅ መስመር ግንባታ ስራ አከናውኗል፡፡
የድሬኔጅ መስመር ግንባታ ስራው ባለፈው ቅዳሜ እና እሁድ የትራፊክ እንቅስቃሴው ላይ ጫና በማይፈጥር ሁኔታ ታቅዶ የተከናወነ ሲሆን፣ የግንባታ ስራው መከናወኑ በአካባቢው በሚከሰት ጎርፍ ምክንያት በእግረኛ፣ በተሽከርካሪ እና በከተማ ቀላል ባቡር እንቅስቃሴ ላይ ይፈጠር የነበረውን ችግር መቅረፍ ያስችላል፡፡
በአካባቢው ይከሰት የነበረውን የጎርፍ ችግር ለመፍታት ባለስልጣኑ ከመጋቢ መንገዶች ወደ ዋናው አስፋልት መንገድ የሚገባ የጎርፍ ውሃን ማስተናገድ የሚችል 300 ሜትር ርዝመት የሚሸፍን የዝናብ ውሃ መፋሰሻ (ድሬኔጅ) መስመር ሙሉ በሙሉ የመቀየር ስራ አከናውኗል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity