+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በቀለበት መንገድ ላይ የአስፋልት ጥገና ስራ እየተከናወነ ነው

ግንቦት 5 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በቀለበት መንገድ ላይ የተጎዱ ቦታዎችን በመለየት የአስፋልት ጥገና ስራ እያካሄደ ይገኛል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በዋና ዋና እንዲሁም በአቋራጭ መንገዶች ላይ ከሚያከናውነው የአስፋልት መንገድ ጥገና ሥራ ጎን ለጎን በቀለበት መንገድ ላይም የመንገድ ጥገና እያከናወነ ይገኛል፡፡

የውስጠኛው የቀለበት መንገድ በየዕለቱ ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት የሚያስተናግድ እና በርካታ ከባድ ተሽከርካሪዎች የሚተላለፉበት ዋና መንገድ ከመሆኑም በተጨማሪ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ በመሆኑ በተለያዩ ቦታዎች ላይ የተቦረቦረው አስፋልቱ ለትራፊክ እንቅስቃሴ አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል፡፡

በመሆኑም አሁን ላይ የተጎዳውን የአስፋልት ክፍል ቆርጦ በማንሳት የጥገና ስራው እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት የጥገና ሥራ ከተከናወነባቸው የቀለበት መንገዱ ክፍሎች መካከል ከጦር ኃይሎች – ዘነበወርቅ እንዲሁም ከዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን – ቦሌ ሚካኤል ድረስ ያሉት አካባቢዎች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

በቀለበት መንገድ እና ከቀለበት መንገድ ውጭ ባሉት የከተማዋ መንገዶች ላይ የሚካሄደው የጥገና ሥራ በቀጣይም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.