+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በጉለሌ ክፍለ ከተማ በላይ ዘለቀ ትምህርት ቤት ጀርባ የድልድይ ግንባታ ስራ በመከናወን ላይ ነው

ግንቦት 1 ቀን 2015 አዲስ አበባ ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በጉለሌ ክፍለ ከተማ በላይ ዘለቀ ትምህርት ቤት አካባቢ የሚገኘውን ነባር ድልድይ አገልግሎት ለማሻሻል በአዲስ በመገንባት ላይ ነው፡፡

ድልድዩ ለረጅም ጊዜ በማገልገሉ ምክንያት በመንገዱ ተጠቃሚዎች ላይ ሊፈጥር የሚችለውን አደጋ አስቀድሞ ለመከላከል በአዲስ መልክ የድልድዩን ግንባታ ማከናወን ጀምሯል፡፡

በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በመከናወን ላይ የሚገኘው ይህ የድልድይ ግንባታ ፕሮጀክት ስራ 10 ሜትር ርዝመት እና 10 ሜትር የጎን ስፋት እንዲሁም ከመሬት 9 ሜትር ከፍታ አለው፡፡

አሁን ላይ በፕሮጀክቱ የአፈር ቁፋሮ፣ የገረጋንቲ ሙሌት እና የግንብ ስራ በመከናወን ላይ የሚገኙ ሲሆን የፕሮጀክቱ ፊዚካል አፈፃፀም 46 በመቶ ላይ ደርሷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.