በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ለሚገነባው ማየት የተሳናቸው ሴት ህፃናት አዳሪ ት/ቤት የመቃረቢያ እና የምድረ ግቢ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ስራ ተጀመረ
ሚያዝያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በቅርቡ የግንባታ ስራው ለሚጀመረው ማየት የተሳናቸው ሴት ህፃናት አዳሪ ት/ቤት የመቃረቢያ እና የምድረ ግቢ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ስራ ተጀመረ፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በየዓመቱ በእቅድ ይዞ ከሚያከናውናቸው መደበኛ የመንገድ መሠረተ ልማት ስራዎች በተጨማሪ፣ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በተለያዩ የመንግሥት አገልግሎት መስጫ ተቋማት የመንገድ ግንባታና ጥገና ስራዎች ሲያከናውን መቆየቱ ይታወሳል፡፡
በያዝነው በጀት ዓመትም አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ለሚገኘው ማየት የተሳናቸው ሴት ህፃናት አዳሪ ትምህርት ቤት የሚያስፈልገውን የመቃረቢያ እና የምድረ ግቢ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ስራ አስጀምሯል፡፡
የግንባታ ስራው በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽ/ቤት አስተባባሪነት በአቃቂ ቃላቲ ክፍለ ከተማ በሚገነባው ማየት የተሳናቸው ሴት ህፃናት አዳሪ ት/ቤት የሚከናወን ሲሆን ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ 1 ኪሎ ሜትር ርዝመት ሲኖረው 3 ሜትር የእግረኛ መንገድን ጨምሮ በ15 ሜትር የጎን ስፋት የሚገነባ ነው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity