+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በክረምት ወቅት የሚከሰት የጎርፍ አደጋን ለመቀነስ ከወዲሁ በበጋ ወቅት ትኩረት ተሰቶ እየተሰራ ይገኛ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24 ቀን 2015ዓ.ም፣- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በክረምት ወቅት የሚከሰት የጎርፍ አደጋ ስጋትን ለመቀነስ የድሬኔጅ መስመር ጥገና እና የፅዳት ስራዎችን በዕቅድ ይዞ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ከእሳት እና ድንገተኛ ስራ አመራር ኮሚሽን ጥቆማ የመጡ 67 የጎርፍ እና 24 የመሬት መንሸራተት አደጋ ሊደርስባቸው ይችላሉ ተብለው ከተለዩ አካባቢዎች ውስጥ 23 የሚሆኑ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ የድጋፍ ግንብ፣ የውሃ መፋሰሻ መስመር ጥገና፣ ፅዳት እና ግንባታ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

ከእነዚህ አካባቢዎች መካከል አለምባንክ ኢንዱስትሪ መንደር፣አንፎ ድልድይ፣ሳንሱሲ ከዳማ ሆቴል ፊትለፊት ፣ አልካን ት/ቤት ፣ከእንግሊዝ ት/ቤት ጀርባ፣የካቲት 66 ት/ቤት እንዲሁም ሌሎች አካባቢዎች ይገኙበታል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የጎርፍ አደጋ ስጋትን ለመቀነስ በቀጣይም 8 የከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የዲዛይን ስራ አጠናቆ ወደ ስራ ለመግባት የቅድመ ዝግጅት ስራ እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን ቀሪ 27 የሚሆኑ የመዲነዋ አካባቢዎች የዲዛይን ስራ እና የወሰን ማስከበር ችግሮችን ለመፍታት በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ባለስልጣኑ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በመዲናዋ ነዋሪዎች ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ 315.8 ኪሎ ሜትር የሚሆን የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር የጽዳትና የጥገና ሥራ አከናውኗል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.