ባለስልጣኑ በ 9 ወራት ውስጥ ከ 600 ኪሎ ሜትር በላይ የግንባታና የጥገና ስራዎችን አከናወነ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 21 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በ2015 በጀት ዓመት ባለፉት 9 ወራት ውስጥ 639.9 ኪሎ ሜትር ልዩ ልዩ የግንባታና የጥገና ስራዎች ለመስራት አቅዶ 606.3 ኪ.ሜ በማከናወን የእቅዱን 94.75 በመቶ ለማሳካት ችሏል፡፡
በበጀት ዓመቱ 9 ወራት ውስጥ ከተከናወኑት የግንባታ ስራዎች መካከል 24.24 ኪ.ሜ የአስፋልት፣ 8.06 ኪ.ሜ የጠጠር፣ 7.69 ኪ.ሜ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ የኮብል መንገዶች፣ 29.16 ኪ.ሜ የኮብል ንጣፍ መንገዶች፣ 11.09 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድመልሶ ግንባታ፣ 0.4 ኪ.ሜ የዲሬኔጅ መስመሮች እና 0.34 ኪ.ሜ የድጋፍ ግንብ ስራዎችን የሚያካትት ሲሆን በድምሩም 80.98 ኪ.ሜ ይሸፍናሉ፡፡
በተመሳሳይ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከግንባታ ስራዎች ጎን ለጎን በተለያዩ ምክንያቶች ለብልሽት የተዳረጉ 65.22 ኪ.ሜ የአስፋልት፣ 25.25 ከ.ሜ የጠጠር፣ 309.4 ኪ.ሜ የድሬኔጅ መስመሮች ፅዳት፣ 6.4 ኪ.ሜ የድሬኔጅ መስመር ዕድሳትና ጥገና፣10.45 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ ጥገናና የከርቭ ስቶን ስራ፣27.79 የእግረኛ መከለያ አጥር አዲስና የጥገና ስራ እንዲሁም 80.79 ኪ.ሜ የመንገድ ቀለም ስራ በማከናወን በጠቅላላው 525.32 ኪ.ሜ የሚሆን ልዩ ልዩ የመንገድ ጥገና ስራዎችን በበጀት ዓመቱ 9 ወራት ውስጥ አጠናቆ ለትራፊክ ክፍት አድርጓል፡፡
ባለስልጣኑ ከዚህ በተጨማሪም በቁጥር 11 ሺ 38 የሚሆኑ ከመንገድ ዳር መብራት ጋር የተያያዙ የጥገና ስራዎችን አከናውኗል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ:- https://www.facebook.com/AbabaCity