+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተሸከርካሪ ግጭት ምክንያት ከ4.2 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የመንገድ መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት ደርሷል

አዲስ አበባ ሚያዝያ 20 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን በተያዘው በጀት ዓመት በዘጠኝ ወራት ውስጥ በተሸከርካሪዎች ግጭት ምክንያት ከ4.2 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የመንገድ መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

ባለፉት ዘጠኝ ወራት 102 የግጭት አደጋዎች በቀለበት መንገድ ላይ ሲከሰት 134 ግጭቶች ደግሞ ከቀለበት መንገድ ውጪ በድምሩ 236 የግጭት አደጋዎች ደርሰዋል፡፡

አብዛኛው ጊዜ በግጭት ጉዳት እየደረሰባቸው የሚገኙት የመንገድ ሀብቶች በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ተገዝተው በምሽት አገልግሎት እንዲሰጡ በተተከሉ የመንገድ መብራት ምሶሶዎች ፣ የትራፊክ ምልክቶች ፣ የአቅጣጫና ርቀት አመላካች ሰሌዳዎች ፣ የእግረኛ መከላከያ አጥሮች ፣ የመንገድ ማካፈያ ግንቦች እና የማንሆል ክዳኖች ላይ ነው፡፡

አሽከርካሪዎች ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ ወጥቶባቸው አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ መንገዶች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ በኃላፊነት በማሽከርከር የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መልዕክቱን ያስታላልፋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ:- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር:- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.