+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በከተማዋ በክረምት ጐርፍ ስጋት የሆኑ አካባቢዎች ተለይተው የማሻሻያ ስራዎች እየተከናወኑ ነው

ሚያዝያ 18 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ለጐርፍ ስጋት ናቸው ተብለው በተለዩ አካባቢዎች ላይ የዝናብ ውሃ መፋሰሻ መስመሮችን ለማሻሻል የፅዳት፣ የጥገና እና የመልሶ ግንባታ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

ባለስልጣን መሰሪያ ቤቱ በያዝነው በጀት ዓመት የድሬኔጅ መስመሮች ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች ተከታታይነት ያለው የፅዳት፣ የጥገና እና ግንባታ ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በክረምት ወቅት ለጐርፍ ስጋት ናቸው ተብለው በጥናት የተለዩ የዝናብ ውሃ መውረጃ መስመሮች የፅዳት፣ የጥገና እንዲሁም የማሻሻያ ዲዛይን ጥናት ስራዎችን በማከናወን እንደ አዲስ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡

በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች የማሳሻያ ስራ ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል ከፍየል ቤት ወደ አያት መንገድ፣ ዓለም ባንክ አርሴማ ሠፈር፣ ሳሪስ አቦ ቀለበት መንገድ በተለምዶ አለቃ ሠፈር፣ ለቡ ቫርኔሮ አካባቢ፣ ቤተል ጊዮርጊስ፣ ጨው በረንዳ አካባቢ፣ ካራቆሬ መብራት ኃይል አካባቢ፣ አማኑኤል ቤ/ክ ፊትለፊት የሚጠቀሱ ሲሆኑ በቀጣይም እስከ ክረምት መግቢያ ድረስ በሌሎች አካባቢዎች የማሻሻያ እና የጥገና ስራዎች የሚከናወን ይሆናል፡፡

በመሆኑም በተለይም በክረምት ወቅት በጎርፍ መጥለቅለቅ ምክንያት የሚደርሱ የመንገድ የሀብት ጉዳቶችና የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይከሰት ሕብረተሰቡ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ወጥቶባቸው የተገነቡ መንገዶችና የመንገድ ዳር የዝናብ ውሃ መፋሰሻ መስመሮችን ከጉዳት በመጠበቅና በመንከባከብ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መልእክቱን ያስተላልፋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ:- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር:- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.