የኤምፔሪያል ማሳለጫ ድልድይ 65 በመቶ ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣መጋቢት 7 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአካባቢውን የትራፊክ መጨናነቅ ችግር ያሻሽላል ተብሎ የታመነበት የኤምፔሪያል ማሳለጫ ድልድይ ግንባታ ከ65 በመቶ በላይ ተጠናቋል፡፡
በአሁኑ ወቅት የማሳለጫ ድልድዩ የቀኝና የግራ መስመሮች ግንባታቸው በከፊል ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ሆነው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የመቃረቢያ መንገዶቹን በቅርብ ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ የሙሌትና የሰብ ቤዝ ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡
ይህ የመንገድ ፕሮጀክት በቻይና ፈርስት ሀይ ዌይ ኢንጂነሪንግ እየተገነባ የሚገኝ ሲሆን የማማከርና የቁጥጥር ስራው በስታዲያ ኢንጂነሪንግ ስራዎችአማካሪ ድርጅት በኩል እየተሰራ ይገኛል፡፡
የማሳለጫ ድልድዩ በአጠቃላይ 1.8 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 40 ሜትር የሚደርስ የጎን ስፋት ያለው ሲሆን ለግንባታው ማስፈፀሚያ ከ714.8 ሚሊዮን ብር በላይ ተይዞለታል፡፡
የማሳለጫ ግንባታው ሲጠናቀቅ አሁን ላይ በአካባቢው ያለውን ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት ከማሻሻሉም ባሻገር የከተማዋን ገፅታ በመሻሻል ለመዲናዋ ተጨማሪ ውበት እንደሚያላብስ ይታመናል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity