በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የአስፋልት ጥገና ስራ እየተከናወነ ይገኛል
አዲስ አበባ፣መጋቢት 11 ቀን 2015ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በተለያዩ የከተማዋ ማዕዘናት እያከናወናቸው ከሚገኙ አዳዲስ የመንገድ ግንባታ ስራዎች ጐን ለጐን አገልግሎት እየሰጡ ከሚገኙ መንገዶች መካከል በተለያዩ ምክንያቶች ለብልሽት የተዳረጉ መንገዶችን በመለየት እንደጉዳት ደረጃቸው የጥገና ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡
በያዝነው ሳምንት የአስፋልት ጥገና ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል ከጥቁር አንበሳ – ሚግሬሽን ፣ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር – ዳሽን ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ፣ከሚሊኒክ ሆስፒታል – ጃንሜዳ ፣ ጎላ ሚካኤል አካባቢ እና ሌሎች የከተማዋ አካባቢዎች ይገኙበታል፡፡