+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

አዲስ አበባ፣መጋቢት 7 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የ36ኛው የአፍሪካ ህብረት

አዲስ አበባ፣መጋቢት 7 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የ36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባኤ እና 42ኛው የአስፈፃሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ በስኬት እንዲጠናቀቅ ላበረከተው የላቀ አስተዋፅኦ ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ልዩ የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከሚያከናውናቸው መደበኛ የመንገድ ግንባታና ጥገና ስራዎች በተጨማሪ ለጉባኤው ድምቀት የሚሰጡና የመዲናዋን ገፅታ የሚገነቡ ልዩ ልዩ የመንገድ አካላት የጥገና ስራዎችን ማከናወኑ ይታወሳሉ፡፡

ባለስልጣኑ በበጀት ዓመቱ ለማከናወን በዕቅድ የያዛቸውን የመንገድ ግንባታና ጥገና ስራዎች ለማሳካት በትኩረት እየሰራ የሚገኝ ሲሆን እስከ በጀት ዓመቱ መገባደጃ ድረስ በግንባታ ሂደት ላይ ከሚገኙ አዳዲስ መንገዶች መካከል የተወሰኑትን ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ በትጋት እየፈፀመ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.