+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በክረምት ወቅት የሚከሰት የጎርፍ አደጋ ስጋትን ለመቀነስ የድሬኔጅ መስመሮች ጥገና እና ፅዳት ስራ በስፋት እየተከናወነ ይገኛል

አዲስ አበባ፣መጋቢት 4 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በአፈር፣ በቆሻሻና መሰል ምክንያቶች የተደፈኑ እና ለብልሽት የተዳረጉ የዝናብ ውሃ መፋሰሻ መስመሮችን በመለየት የፅዳት እና የጥገና ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡

በክረምት ወቅት በውሃ መፋሰሻ መስመሮች መደፈን ምክንያት የጎርፍ አደጋ ስጋት ከመከሰቱም ባሻገር መንገዶችም ለብልሽት ይዳረጋሉ።

በመሆኑም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በክረምት ወቅት የሚከሰተውን ችግር ለመቅረፍ የድሬኔጅ መስመር ጥገና እና ፅዳት ስራ በበጋው ወቅት በስፋት ሲያከናውን ቆይቷል፡፡

በዚህም መሰረት እስከ የካቲት ወር መጨረሻ ድረስ 303.27 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የድሬነጅ መስመር የፅዳት እና የጥገና ስራ አከናውኗል። ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ ምክንያቶች ለብልሽት የተዳረጉ በቁጥር 1274 የማንሆል ክዳኖችን በመቀየር ለአገልግሎት አብቅቷል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በበጀት ዓመቱ ለማከናወን በዕቅድ ከያዛቸው የድሬኔጅ ፅዳትና ጥገና ሥራዎች በተጨማሪም ከእሳት እና ድንገተኛ ስራ አመራር ኮሚሽን የሚመጡ ጥቆማዎችን ጨምሮ የጎርፍ አደጋ ስጋት አካባቢዎችን አካቶ እየሰራ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.