+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የባለስልጣኑ ሰራተኞች ዓለም አቀፍ የሴቶችን ቀንን አከበሩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1 ቀን 2015ዓ.ም፡-የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ሰራተኞች በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ112ኛ፣ በኢትዮጵያ ለ47ኛ ጊዜ የተከበረውን ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን ‹‹እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ›› በሚል መሪ ቃል አክብረዋል፡፡

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ዋና ዳይሬክተር በመወከል በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የህግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ውብዬ ማርዬ በመክፍቻ ንግግራቸው በሀገራችን ግማሹን ቁጥር የሚይዙት ሴቶች በመሆናቸው ያለነሱ ተሳትፎ የሀገር እድገት እውን ስለማይሆን ሴቶችን በማብቃትና በተለያዩ የስራ መስኮች በማሳተፍ በኢኮኖሚውም ሆነ በአመራርነት ደረጃ አውንታዊ ለውጥ ማምጣት ይችላሉ ብለዋል፡፡

በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሴቶች እና ወጣቶች ጉዳይ ቡድን መሪ ወ/ሪት ፀደንያ አበበ በበኩላቸው ሁላችንም የሴቶች ጠባቂነን ስንል እህቶቻችን ላይ የሚደርሰውን ፆታዊ ጥቃት እንዲሁም ማህበራዊ ጫና መከላከል እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ወ/ሪት ፀደንያ አያይዘውም የሴቶችን ሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን በማክበር ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋጋገጥ ይገባል ብለዋል፡፡

በመጨረሻም በተያዘው በጀት ዓመት የአገልግሎት ጊዜያቸው አጠናቀው በጡረታ ለተገለሉ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሴት ሰራተኞች የምስጋና እና እውቅና የመስጠት መርሀ-ግብር ተከናውኗል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.