የለቡ ማሳለጫ ድልድይ ሌላኛው የከተማዋ ፈርጥ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 29 ቀን 2015 ዓ.ም፡- በአዲስ አበባ ከተማ ለቡ መብራት ኃይል እየተገነባ የሚገኘው ግዙፍ የማሳለጫ ድልድይ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሲጠናቀቅ ትራፊኩን ከማሳለጡም በተጨማሪ ለአካባቢው ልዩ ገፅታን እንደሚያላብስ ይታመናል፡፡
በአሁኑ ወቅት የድልድዩ ግንባታ በመገባደድ ላይ የሚገኝ ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥም ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የማንሆል ግንባታ፣ የመቃረቢያ መንገዶች የድሬኔጅ መስመር ዝርጋታ፣ የገረጋንቲ አፈር ሙሌት እና የሰብ ቤዝ ስራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡
ይህ የመንገድ ፕሮጀክት በቻይና ፈርስት ሀይ ዌይ ኢንጂነሪንግ እየተገነባ የሚገኝ ሲሆን የማማከርና የቁጥጥር ስራው በስታዲያ ኢንጂነሪንግ ስራዎች አማካሪ ድርጅት እና በጂ ኤንድ ዋይ ኮንሰልቲንግ ኢንጅነርስ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በኩል እየተሰራ ይገኛል፡፡
የማሳለጫ ድልድዩ አጠቃላይ 1.1 ኪ.ሜ ርዝመትና 40 ሜትር የሚደርስ የጎን ስፋት ያለው ሲሆን ለግንባታ ወጪውም ከ634 ሚሊዮን ብር በላይ ተይዞለታል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity