+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በከተማዋ የተለያዩ ማዕዘናት የመንገድ ዳር መብራት ጥገና ተከናውኗል

አዲስ አበባ፣የካቲት 28 ቀን 2015ዓ.ም፣- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከመንገድ ግንባታ እና ጥገና በተጨማሪ የከተማዋ የነዋሪዎች የምሽት እንቅስቃሴ የተሳካ ለማድረግ በተለያዩ ምክንያቶች የተበላሹ እና ነባር የመንገድ ዳር መብራቶችን የማዘመን እና የመጠገን ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት የመንገድ ዳር መብራት ጥገና ከተከናወነባቸው የከተማዋ አካባቢዎች መካከል ከለገሃር – ጨርቆስ፣ ከጦርሀይሎች ሆስፒታል – ልደታ ፍርድ ቤት፣ ከልደታ ፀበል – ኮካ -ተክለሀይማኖት፣ ምናዬ ህንፃ – ካርል አደባባይ ፣መገናኛ – ቀበና – አራት ኪሎ ፣ ሜክሲኮ ደብረወቅ ህንፃ አካባቢ፣ቡልጋሪያ ሚካኤል ቤተክርስቲያን፣ ማዘጋጃቤት አካባቢ እና ሌሎችም የከተማዋ አካባቢዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ይሁን እንጂ በከፍተኛ ወጪ በተሰሩ የመንገድ ዳር መብራቶች ላይ የትራንስፎርመር ፣የኬብል፣ የብሬከር እና የፊዊዝ ስርቆት እንዲሁም በተሸከርካሪ ግጭት ሳቢያ በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች የመንገድ መብራት አገልግሎት መቆራረጥ እያጋጠመ ይገኛል፡፡

በመሆኑም ህብረተሰቡ የመንገድ ዳር መብራቶችን ከጉዳትም ሆነ ከስርቆት መጠበቅ የራሱን ህይወት ከአደጋ መጠበቅ መሆኑን በመረዳት በአግባቡ እንዲገለገልባቸው ባለስልጣኑ መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.