ቦሌ አራብሳ5 ኮንዶሚኒየም ሎት1 እና 2 የመንገድ ግንባታ የወሰን ማስከበር ስራው በወቅቱ ባለመጠናቀቁ ፕሮጀክቱ በታሰበው ፍጥነት እንዳይከናወን ተፅኖ አሳድሯል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 28 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ቦሌ አራብሳ 5 ሎት 1 እና 2 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ የወሰን ማስከበር ስራው ባለመጠናቀቁ በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ እንቅፋት ሆኗል፡፡
የመንገዱን ግንባታ እያከናወነ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽ ስራዎች ኮርፖሬሽን የስራ ተቋራጭ ሲሆን ሀማንዳ ኢንጂነሪንግ አማካሪ ድርጅት ደግሞ የማማከርና የቁጥጥር ስራውን እየተከታተለው ይገኛል፡፡
በሁለት ሎት ተከፍሎ የግንባታ ስራው በመከናወን ላይ የሚገኘው ይህ የመንገድ ፕሮጀክት በአጠቃላይ አስፋልት እና ኮብልን ጨምሮ 25.23 ኪ.ሜትር ርዝመት የሚሸፍን ሲሆን በአማካኝ ከ10-30 ሜትር የጎን ስፋት የሚሸፍን ነው፡፡
አሁን ላይ 11.7 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍነው የመንገዱ ክፍል የአፈር ቆረጣ ስራ እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን 1.1 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የመንገዱ ክፍል ደግሞ የሰቤዝ ስራ ተጠናቋል እንዲሁም ፣የከርቭስቶን ፣ የፓይፕቀበራ እና ሌሎች ተያያዥ ስራዎችም እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡
የመንገድ ፕሮጀክቱ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በመንገዱ ወሰን ውስጥ የሚገኙ ቀሪ የወሰን ማስከበር ስራዎችን በማጠናቀቅ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity