+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የከተማዋን የመንገድ ሽፋን ለማሳደግና የትራፊክ ፍሰቱን ይበልጥ ምቹ ለማድረግ በየዓመቱ

በከፍተኛ በጀት የመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራዎችን በማከናወን የከተማችንን ነዋሪዎች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሠራ ይገኛል።

ይሁን እንጂ በመንገድ ሀብት አጠቃቀም ጉድለትና ኃላፊነት በጎደለው ህገወጥ ተግባራት ሳቢያ በመንገድ ሀብታችን ላይ በየጊዜው እየደረሰ ያለው ጉዳት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።

በተለይም በእግረኛ መንገዶች ላይ እየተፈፀመ ያለው የመንገድ መብት ጥሰት የችግሩን አሳሳቢነት አጉልቶ ከሚያሳዩ አይነተኛ አመላካቾች መካከል አንዱ ነው።

በእግረኛ መንገዶች ላይ ከሚፈፀሙ የተለያዩ ህገወጥ ተግባራት መካከል በእግረኛ መንገዶች ላይ መኪና ማቆም እና ማሽከርከር እንዲሁም በእግረኛ መንገድ ላይ መኪና አቁሞ እቃ መጫን እና ማውረድ ይጠቀሳል።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በአዋጅ የተሰጠውን ሥልጣንና ኃላፊነት መሠረት በማድረግ በመንገድ ሀብት ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ህገወጦችን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ የሚያካሂደው እንቅስቃሴ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በየደረጃው የሚገኙ የአስተዳደርና የፀጥታ አካላት እንዲሁም የሚመለከታቸው ሌሎች ባለድርሻዎች በመንገድ አካላት ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ህገወጦችን በመከላከል ረገድ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ባለሥልጣን መስሪያቤቱ ጥሪውን ያቀርባል።

የተሻለ መንገድ ለተሻለች አዲስ አበባ፤

Comments are closed.